የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ በታች በተገለጸው ክፍት የስራ መደብ ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል። የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ I ብዛት፡ 1 ደመወዝ፡ 3,526 የትምህርት ዝግጅት፡ የመጀመሪያ ዲግሪ ጆርናሊዝምና ኮሙዩኒኬሽን፣ በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ በፌደራሊዝም፣ በቋንቋና ስነ-ጽሁፍ የትምህርት መስኮች የወሰደ አግባብ ያለው የስራ ልምድ፡ 0 ዓመት ማሳሰቢያ፡ - የስራ ቦታ፡ አዲስ አበባ - የመመዝገቢያ ቦታ፡ እርቼ ከስቴዲየም ወደ ግሎባል መሄጃ መንገድ 2ኛ የባቡር ፌርማታ መውረጃ የቀድሞ ኮንስራክሽን ሚኒስቴር የነበረው ህንፃ ቢሮ ቁጥር 505 - የምዝገባ ቀን፡ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ነው። - አመልካቾች የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። - በስራ ልምድ የምትወዳደሩ አመልካቾች የስነ-ምግባር ማስረጃ ማቅረብ አለባችሁ። - ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ!