በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባሉት ክፍት የስራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል። የስራ መደብ መጠሪያ፡ የሰው ኃይል ሙሌትና የስራ ምዘና ባለሙያ ደመወዝ፡ 9,246 የትምህርት ዝግጅት፡ በማኔጅመንት፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን እና ዴቨሎፕመንት ማኔጅመንት፣ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም፣ በአድሚኒስትሬቲቭ ሰርቪስ ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ፣ በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ በመልካም አስተዳደርና ልማት ጥናት፣ በሰው ሀብት ስራ አመራር የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ብዛት፡ በሰው ሃብት ስራ አመራርና ልማት ኦፊሰር፣ ጀ/ኦፊሰር፣ በትምህርትና ስልጠና ኦፊሰር፣ በሰው ሀብት መረጃ አስተዳደር ኦፊሰር፣ ጀ/ኦፊሰር፣ በሰው ኃይል ሙሌትና አገልግሎት ጀ/ኦፊሰር፣ በአደረጃጀት፣ ስራ ምዘናና ጥቅማ ጥቅም ጥናት ኦፊሰር በሰው ሃብት መረጃ አሰባሰብና ጥንቅር ሰራተኛ 2 ዓመት ብዛት፡ 1 ስለሆነም ከዚህ በታች በተመለከተው ክፍት የስራ መደብ ላይ የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 6 (ስድስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ፡ 1. ለስራ መደቡ የምታመለክቱ አመልካቾች ከምትሰሩበት መስሪያ ቤት የስነ-ምግባር ችግር እንደሌለበት የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባኋል። 2. አመልካቾች ለምዝገባ ስትመጡ የትምህርት ማስረጃችሁን ኦሪጅናል ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባችሁ። 3. የሚቀርበው የስራ ልምድ ከግል መ/ቤት የተገኘ ከሆነ የስራ ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 4. የኮሌጅ ዲፕሎማ ወይም በቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ተመራቂዎች የብቃት ሰርተፍኬት COC ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። 5. የምዝገባ ቦታ መገናኛ ለም ሆቴል ኮሜት ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 906 ስልክ ቁጥር 011 667 49 97