ብሔራዊ የቆላ ዝንብና ገንዲ በሽታ መቆጣጠሪያና ማጥፊያ ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች በተጠቀሰው ክፍት የስራ መደብ ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰራተኞችን በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል። የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የስራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት ባለሙያ ደመወዝ፡ 3,653 ብዛት፡ 1 የትምህርት ደረጃ፡ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ዓይነት፡ በአካባቢ ጤና ሳይንስ (Occupational Safety and Professional) የስራ ልምድ፡ 0 ዓመት የስራ ቦታ፡ አዲስ አበባ ማሳሰቢያ፡ - የቅጥር ሁኔታ፡ በቋሚነት - ከዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ በላይ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ማመልከት ይችላሉ። - በሌቭልና በዲፕሎማ የምታመለክቱ ተወዳደሪዎች የብቃት ማረጋገጫ (COC) ማቅረብ ይኖርባችኋል። - የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ወደፊት ይገልጻል። - አመልካቾች ለምዝገባ በሚመጡበት ሰዓት ኦሪጅናልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል። - ከግል ተቋማት የሚቀርቡ የስራ ልምድ ግብር የተከፈለበት መሆን አለበት። የመመዝገቢያ ቦታ እና ለተጨማሪ መረጃ፡ - ብሔራዊ የቆላ ዝንብና ገንዲ በሽታ መቆጣጠሪያና ማጥፊያ ኢንስቲትዩት፡ ልዩ ቦታ ቃሊቲ ገብርኤል ከ40/60 ኮንዶሚኒየም ጀርባ የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 ስልክ ቁጥር፡ 011 4 39 62 82