ጀማሪ ጸሃፊ at NIB CANDY FACTORY PLC
Position Title: ጀማሪ ጸሃፊ
Employer: NIB CANDY FACTORY PLC
Employment: Full-Time | Permanent
Place of Work: Burayu industry zone/Tatek/ - Ethiopia
Salary: Negotiable
Posted date: 1 day ago
Deadline: November, 23/2025 (8 days left)
ዋና ዋና ተግባራት
- ከረቂቅ ወይም ኦርጅናል ላይ በኮምፒዩተር ታይፕ ማድረግ፣ መልዕክት መቀበል፣ ማስተላለፍ፣ እንግዳ መቀበል፣ ማስተናገድ፣ ሌሎችንም የቢሮ ሥራዎች ማከናወን፡፡
ዝርዝር ተግባራት
- ከረቂቅ ወይም ኦርጂናል ላይ በሚሰጣት መመሪያ መሠረት ደብዳቤዎችንና ሌሎችንም ትጽፋለች፤
- የእንግዶችን የስልክ ጥሪዎች በሥነ ሥርዓት በትህትና ትቀበላለች፣ መልዕክት ትቀበላለች፣ ታስተላልፋለች፤
- ከሥራ ክፍሉ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን ድርጅቶችና ግለሰቦች የስልክ ቁጥርና አድራሻ ትይዛለች፤
- እንደአስፈላጊነቱ ደብዳቤ አርቅቃና ታይፕ አድርጋ ለፊርማ ታቀርባለች፤
- ለሥራ ክፍሉ የሚስፈልጉና ለሥራ ክፍሉ የሚደርሱ ሰነዶችንና ደብዳቤዎችን ትይዛለች፣ ፋይል ታደርጋለች፤
- በሥራ ክፍሉ ውስጥ ከሚገኙ ሠራተኞች የሚሰጧትን የጽህፈት ሥራዎች ታከናውናለች፤
- ድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የሥራ ክፍሎችን ሥራ አከፋፍሎ ማሠራት ሲያስፈልግና ስትታዘዝ የሚሰጣትን የጽሕፈት ሥራዎች ታከናውናለች፤
- በተጨማሪም ከቅርብ ኃላፊዋ የሚሰጣትን መመሪያና ትዕዛዝ ታከብራለች፣ ትፈጽማለች፡፡
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ
- በክሬታሪያል ሳይንስ ወይም በቢሮ አስተዳደር ቢኤ ዲግሪ ወይም በደረጃ 4 የተመረቀች ሲ.ኦ.ሲ.ማቅረብ የምትችል
- በሙያዉ ቢያንስ ከአንድ እና ሁለት ዓመት በፋብሪካ ዉስጥ የሰራች
- አመልካቾች አማርኛ፤ኦሮምኛ እና እንግሊዝኛ መስማት፤ መናገርና ማንበብ መቻል ይኖርባቸዋል
የስራ ቦታ ቡራዩ ኢንደስትሪ ማዕከል /ታጠቅ/
የቅጥር ሁኔታ -የሙከራ ጊዜዉን በአጥጋቢ ሁኔታ ለሚያጠናቅቅ በቋሚነት
ጾታ -ሴት
ደሞዝ ፡ በስምምነት
How to apply
አመልካቾች የስራ ልምድና የትምህርት ማስረጃችሁን በመያዝ
ከዉንጌት አደባባይ ወደ አስኮ በሚወስደዉ መንገድ ከእርግብ ሆቴል ፊት ለፊት ንብ ከረሜላ ፋብሪካ ዋናዉ መስሪያ ቤት እሰከ
ህዳር 15 2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ የሰዉ ሃይል አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ
ወይም በኢሜል አድራሻ
demanu.hr@nibcandy.com
መላክ ትችላላችሁ፡፡ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር
0112623828 መደወል ትችላላችሁ፡፡
Don’t have a winning CV? Let GeezJobs write it for you! 👉 CLICK & Learn about the Service