
Driver I: Mizan Teferi Branch at Abyssinia Bank
Position Title: Driver I: Mizan Teferi Branch
Employer: Abyssinia Bank
Employment: Full-Time | Permanent
Place of Work: Mizan Teferi - Ethiopia
Posted date: 10 hours ago
Deadline: September, 26/2025 (4 days left)
Qualification
- EDUCATION: 12th/10th Grade Complete, and Public I or Third-level Driving License.
- EXPERIENCE: Minimum of 2 Years of Driving experience. Experience in the banking industry is advantageous
የሥራ ዓላማ
ለስራ ወደ ተለያዩ ስፍራዎች የሚንቀሳቀሱ የባንኩን ሰራተኞች ወይም ዕቃ/ንብረት ከቦታ ቦታ ማጓጓዝና በኃላፊነት የተሰጠውን ተሽከርካሪ በአግባቡ እና በጥንያቄ በመያዝ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይሆናል፡፡
ዝርዝር ተግባራት:
- ሥራ ከመጀመሩ በፊት የሞተር ዘይት፣ ውሃ፣ መብራት፣ የጎማ ነፋስና የመሳሰሉትን ነገሮች መሟላታቸውን ማረጋገጥ።
- የባንኩን ከባድ፤ መካከለኛ፤ አነስተኛና ቀላል ተሽከርካሪዎች በመያዝ በከተማም ሆነ ከከተማ ውጭ ሠራተኞች ወይም ዕቃ በማጓጓዝ አገልግሎት መስጠት።
- ለተሽከርካሪው የሚያስፈልጉ ነገሮች እንደ ነዳጅ፣ መጠባበቂያ ጎማና የመፍቻ ዕቃዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ።
- በመስክ ሥራ ላይ ለተሽከርካሪው የሚያስፈልጉ ነገሮች እንደ ነዳጅና ሌሎች ዕቃዎችን ሲያስፈልጉ በህጋዊ ደረሰኝ መግዛት፤ እንዲሁም ማወራረድ።
- ጉዞ ከመጀመሩ በፊትና ከጨረሰ በኋላ የተሽከርካሪው የኪሎ ሜትር ቆጣሪ መነሻና መድረሻ ቁጥሮችንና የሄደባቸው ቦታዎችን በተዘጋጀው ቅጽ ወይም ፎርም ላይ መመዝገብ።
- ለተሽከርካሪው የሚያስፈልጉትን መለዋወጫና እድሳት በመከታተል ለክፍል ኃላፊው ወይም ለትራንስፖርት አስተዳደር በወቅቱ ማሳወቅ።
- አነስተኛ ጥገናዎችን ያከናውናል፤ ከአቅም በላይ የሆነ ብልሽት ሲያጋጥም ሁኔታውን ወዲያው ለትራንስፖርት አስተዳደር ማሳወቅ።
- እንዲያደርስ የተረከበውን ንብረት በአግባቡ ቆጥሮ ለሚመለከተው አካል ማስረከብ።
- የተረከበውን ተሽከርካሪ ደህንነት በሚገባ መጠበቅ።
- ተሽከርካሪው በብልሽት ምክንያት ለጥገና ጋራዥ ሲገባ ክትትል ማድረግ ፤ በትክክል መሠራቱንም ማረጋገጥ፤ እንደአስፈላጊነቱም ሁኔታውን ለክፍል ኃላፊው ወይም ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ማሳወቅ።
- ተሽከርካሪው በወቅቱ ሰርቪስ እንዲደረግለት መጠየቅ።
- ተሽከርካሪውን በየዓመቱ ማስመርመር።
- ቦሎና ሌሎች እንዲለጠፉ የተጠየቁ ሰነዶች በተፈቀዱ የሽከርካሪው አካል ላይ መለጠፍ።
- በስራ ሰዓት የባንኩን የደንብ ልብስ ንጽህናውን ጠብቆ መልበስ::
- ከቅርብ የስራ ሀላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን ማከናወን።