No worries! You can check out similar opportunities — Just Click Below.
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተገለጸው የስራ መደብ ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል። የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ባለሙያ I ደረጃ፡ VIII ተፈላጊ ችሎታ፡ ጆርናሊዝምና ኮሙዩኒኬሽን፣ በጋዜጠኝነት፣ በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ በቋንቋና ስነጽሁፍ፣ በስነጽሁፍ፣ በቋንቋ/በአማርኛ እና እንግሊዘኛ፣ በኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት፣ ህዝብ ግንኙነት፣ አለም አቀፍ ግንኙነት፣ በሚዲያ፣ በቋንቋና ፎሪን ላንጉጅ ሊትሬቸር፣ ኢትዮጵያን ላንጉጅ ሊትሬቸር፣ ፎክለር የተመረቀ ሆኖ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ሙያ መሰረታዊ ስልጠና የወሰደ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ 0 ዓመት ክፍት የስራ መደብ ብዛት፡ 1 (አንድ) ደመወዝ፡ 3,526 ማሳሰቢያ፡ - ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ። - የትምህርት ዝግጅትም ሆነ የስራ ልምድ ቀጥታና አግባብነት ያለው ሊሆን ይገባል - በተመጣጣኝ ዋጋ ለሰራተኞች የካፍቴሪያ አገልግሎት ይሰጣል - በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት የሰርቪስ አገልግሎት ይሰጣል - ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶች የደረጃ /Level/ ተመራቂዎች የብቃት ማረጋገጫ /COC/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል - አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃችሁን በመያዝ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ በሚወስደው መንገድ ባለው በዩኒቨርስቲው ዋናው ግቢ በሚገኘው የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 123 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን - በተጨማሪም በዩኒቨርስቲው ዌብሳይት ላይ መመልከት ትችላላችሁ http://www.ecsu.edu.et/ የዩኒቨርስቲው የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት - ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት 2:15 - 6:15 ከሰዓት 7:15 - 11:15 - አርብ ጠዋት 2:15 - 5:45 ከሰዓት 7:45 - 11:15 ስልክ ቁጥር፡ 011 6 46 23 47 ፖ.ሳ.ቁ፡ 5648